Amharic Code of Conduct

የስነ-ምግባር ደንብ

 

ውድድር

በሁሉም የኒው ዮርክ ሯጮች (“NYRR”) ዝግጅት ለተሳታፊዎች ለበጎፈቃድ ሰራተኞች፣ ለዝግጅቱ ሰራተኞች፣ ተመልካቾችና ለማህበረሰቡ አባላት በስነስርአት ክብር መስጠት ያለባቸውና የውድድሩን ደንቦች መከተል አለባቸው፡፡ በዙሪያ ያሉ ነገሮችንና የዝግጅቱ ኃላፊዎችን ማስታወቂያና መመሪያዎች መረዳትን ጨምሮ ተገቢው የውድድር ስነስርአቶች ሁሌም መከበር አለባቸው፡፡

ስፖርታዊ ያልሆነ ባህሪ

በ NYRR የውድድር ደንቦች ስር ባይጠቀስም ሯጮች ማንኛውም የንግግር ወይም መጥፎ ተግባር ማለትም ትንኮሳ፣ ስድብ ወይም አጸያፊ ድርጊቶች ላይ መሳተፍ የለባቸውም፡፡

ሯጮች በቅድመ-ውድድር ማስታወቂያውና በብሔራዊ መዝርሙር ግዜ በጸጥታ መቆየት ይኖርባቸዋል፡፡

መጀመር

እባክዎን የመወዳደሪያ ቁጥርዎን ይውሰዱና ወደ መስመርዎ ይግቡ፡፡ ወደ ተሰየሙበት መስመር ብቻ ይግቡ፡፡

የጆሮ ማዳመጫዎች

የጆሮ ማዳመጫ በጭራሽ የሚበረታታ አይደለም፡፡ የጆሮ ማዳመጫ ለማድረግ ከመረጡ፣ እባክዎን ሌሎች ተሳታፊዎችን ጨምሮ አካባቢዎች ከተረዱና ሁሉንም ማስታወቂዎች ከሰሙ በኋላ ያድርጉ፡፡

ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች

በዝግጅቱ ላይ ሲሳተፉ ሩጫዎትን ለመከታተል ካልሆነ በስተቀር ከዝግጅቱ በኋላ የሚሆኑ ሌሎች መሳሪያዎችን መጠቀም በጭራሽ አይበረታታም፡፡ 

የሩጫ አካሄድ

ስብጥር፡፡ ሶስት ወይም ከዛ በላይ ጎን ለጎን ሆኖ አለመሮጥ፤ ስፋት ያለው ቡድን የሌሎች ሯጮችን መንገድ ይዘጋል፡፡

መተላለፍ፡፡ ሯጮችን ሲያልፉ መነጋገር እንዲሁም ሌሎች እንዲያልፉ መፍቀድ፡፡ ከኋላዎ የሚሮጥ ሰው “በግራህ” ካልዎት ሯጩ እንዲያልፍ ወደ ቀኞት ገለል በማለት መንገድ ይልቀቁለት፡፡ አንድ ሰው “በቀኝህ” ካለ ወደ ግራዎት ገለል በማለት መንገድ ይልቀቁለት፡፡

መቆም፡፡ በድንገት አይቁሙ፡፡ በድጋፍ ጣቢያው ለመጠጣት ከፈለጉ፣ መጋጨትን ለማስቀረትና ወደፊት ለመሄድ ከጠረጴዛው ላይ በርቀት ያለውን ውሀ ይውሰዱ፡፡ የጫማዎትን ክር ለማሰር ከፈለጉ፣ የመንገዱን ዳር ይያዙ፡፡

መትፋት፡፡ ሲተፉ ወይም ሲናፈጡ ሌሎች ተሳታፊዎችን እንዳይነኩ ይጠንቀቁ፡፡

ማገዝ፡፡ በሩጫ ላይ እያለ ችግር የደረሰበት ሰው ካጋጠምዎት ድጋፍ ያድርጉ እና/ወይም በአቅራቢያዎት ላለ የድጋፍ ጣቢያ፣ ላዘጋጆቹ ወይም በድንገተኛ ስልክ 866-705-6626 ቢሆን ያሳውቁ፡፡

ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች

እባክዎን ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶቹን ሰልፍ ጠብቀው ይጠቀሙ፡፡ በሰልፍ መሀል ጣልቃ አይግቡ፡፡ ከእርስዎ በኋላ መጸዳጃ ቤቶቹን ለሚጠቀሙ ሰዎችም አክብሮት ይኑርዎት፡፡ በመደቡ፣ በመረማመጃው ወይም በመቀመጫው ላይ መሽናት ወይም መበከል፣ ነውር ብቻ ሳይሆን የ NYRR የውድድር ደንቦችንም ይጣረሳል እንዲሁም በነዚህ ድርጊቶችዎ የተነሳ ከውድድሩ ሊወጡ ይችላሉ፡፡

የውድድር ልብስ

ወንድ ሯጮች እራቁታቸውን እንዲሮጡ እና/ወይም በውድድሩ ግዜ ከናቴራቸውን እንዲያወልቁ በጭራሽ አናበረታታም፡፡

ቁሻሻ

ሁሉንም ቆሻሻዎች በድጋፍ ጣቢያው ጨምሮ ባሉ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ውስጥ መጣል፡፡ በድጋፍ ጣቢያው ኩባያዎችን ሲጥሉ ሌሎች ተሳታፊዎችን እንዳይመቱ በጥንቃቄ መሆን አለበት፡፡

ጠፍተው የተገኙ ንብረቶች

በዝግጅቱ ግዜ ወይም ከዛ በኋላ የሰው ንብረት ቢያገኙ እባክዎን ወደ NYRR ድንኳን ወይም ወደ ማንኛውም NYRR ዝግጅት ሰራተኛ ወስደው ይስጡ፡፡ NYRR በቀጣዩ ቀን በ NYRR የሩጫ ማእከል 320 West 57th Street እንዲገኝ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ከተገኙ 30 ቀን የሞላቸው እቃዎች ባለቤቱ ካልመጣ የሚወገዱ ይሆናል፡፡